ሐሙስ 4/7/2017 ዓ.ም
ሰበር ዜና
እንኳን ደስ ያላችሁ ፤ እንኳን ደስ ያለን
የመዝገበ ብርሃን እና ሰላም ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ አበባ ት/ቢሮ በተዘጋጀው በ2017ዓ.ም በአንደኛ መንፈቅ ዓመት KPI እና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ምዘና 98.1 ውጤት በማምጣት ከልደታ ክ/ከተማ ካሉ 21 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች 1ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆነናል።
ይህ ውጤት በዓመቱ በአንደኛ መንፈቅ ዓመት በተቋም ደረጃ በተማሪ ውጤት፣ ስነ-ምግባር እንዲሁም አጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሁሉም መምህራንና ሰራተኛ የተገኘ የልፋት ውጤት ነው።
በመሆኑም ለዚህ ውጤት መሳካት ር/መምህራን፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ አስተዳደር ሰራተኞ፣ ወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊና ባለሞያዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ ፤ እንኳን ደስ አለን።
መዝገበ ብርሃን እንደስማችን እንደ ብርሃን ፍጥነት እውቀትን እየፈነጠቅን፤ መልካም ምግባር እየቀረፅን ለተማሪዎቻችን አርአያ ሆነን አንድ ወደፊት ከፍ ብለን እናሳያለን።


.